ወደ ስቶክሆልም የቋንቋ ት/ቤት እንኳን ደህና መጡ!

የስቶክሆልም የቋንቋ ት/ቤት በህግ የሚተዳደር የግል ት/ቤት ሲሆን ለማንኛዉም ዜጋ ክፍት ነው። ስራውንም የጀመረው እ.ኤ.አ በ2001 ዓ.ም ከ 0 እስከ 9ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን በመቀበል ነው።

ት/ቤቱ ትኩረት የሚያደርገው በቋንቋ ላይ ነው። ይህም ማለት ለተማሪዎቹ ተጨማሪ የሲዊድንኛና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ከ 0 ክፍል ጀምሮ ይሰጣል።በተጨማሪም የኮምፒውተር ትምህርት ይሰጣል።

ት/ቤቱ የተማሪዎቹን ችሎታ ለማጠናከር ስለሚፈልግ የተለያዩ የሞራልና የግብረገብ ጥያቄዎችን በማንሳትና በተጨማሪም በህብረተሰቡ ውስጥ ያለውን የግለሰብ ነጻነት ያስተናግዳል። ለተማሪዎቹም በግልም ሆነ በህብረት እራሳቸውን እንዲችሉ ማድረግና ዕውቀትን በጥራት ማስተላለፍ ዋነኛ ዓላማው ነው። በተጨማሪም ተማሪዎቹ ምቾት እንዲሰማቸውና ደስተኛ እንዲሆኑ ያደርጋል። ይኸውም ደስተኛ ተማሪ ብዙ ዕውቀት ይገበያል ብሎ ስለሚያምን ነው።

እ.ኤ.አ. ከ 2005 ዓ.ም ጀምሮ ት/ቤቱ የፖርፎልዮ አሰራር ጀምሮል። ፖርፎልዮ ማለት አስተማሪው ተማሪዎችና ወላጆች የተማሪውን የዕውቀት እድገት በጋራ የሚገመግሙበት፣ ተማሪዎቹ የሚያስፈልጋቸውን የሚከታተሉበትና የሚያስፈጽሙበት አሰራር ነው። የፖርፎልዮ አላማ ተማሪዎቹ የመማርና የትምህርት ውጤታቸውን ሀላፊነት እንዲወስዱ ማድረግ ነው። በፖርፎልዮ ውስጥ ከዓመት ወደ ዓመት የተማሪዎችን ስኬትና እድገት የሚያሳይ አሉታዊ ነገሮችን በመሰብሰብ የተማሪዎቹን በራስ መተማመን እንዲጠነክር እንፈልጋለን።

ት/ቤቱ ከወላጆች ጋር ጥብቅ ግንኙነት አለው። ስለ ተማሪዎቹ እድገት ለመነጋገርና የወላጆች ስብሰባ በተርም ቢያንስ ሁለት ጊዜ ወይም ከዝያ በላይ ይጠራል። ወላጆች መጥታችሁ ብትጎበኙን ምንግዜም በራችን ክፍት መሆኑን እየገለጽን፣ ማንኛውም ት/ቤቱን ለመጎብኘት ፍላጎት ያለውን ሰው ሁሉ እናስተናግዳለን።ጎብኝዎቻችን ከመምጣታችሁ በፊት ቅድማችሁ ብታሳውቁን ለአሰራራችን አመች ይሆናል። አድራሻችን

 

Stockholms Språkskola
Rågsveds skolgränd 8
Tel. 08-6058070, 070-7331047
www.stockholmssprakskola.org